የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሰላም ስምምነቱን እስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በሰሜኑ የሐገራችን ክፍል ተከስቶ የነበረውን የእርስበርስ ጦርነት ለማቆም ሲደረግ የነበው የሰላም ውይይት ስምምነት ላይ በመድረሱ ለመላው ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የ«እንኳን ደስ አላችሁ» መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለሐገራችን ዘላቂ ሰላም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ብሔር፣ ዘር፣ ቀለምና ሃይማኖት ሳይለይ በጋራ ጠንክሮ መሥራት እንዳለበት ገልጸዋል። በጦነቱ ሕይወታቸው ላለፈ ወገኖች የአላህን እዝነት፣ ለቤተሰቦቻቸው ደግሞ መጽናናትን ተመኝተው ከቀያቸው የተፈናቀሉትን መልሶ በማቋቋሙ ሂደት ላይም በተለይ ህዝበ ሙስሊሙ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ በሚወጡ መርሐ ግብሮች ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

«አፍሪካዊ መፍትሄ ለአፍሪካ ችግሮች» በሚለው መርሕ መሠረት በደቡብ አፍሪካ ለ10 ቀናት ሲካሄድ የነበረውን ድርድር ላመቻቹት የአፍሪካ መሪዎች፣ ለተወከሉት ተደራዳሪዎች እንዲሁም ለአፍሪካ ሕብረት የላቀ ምስጋና አቅርበዋል::

إصدار بيان من المجلس الأعلى للشؤون الإسلامية في أثيوبيا بشأن اتفاقية السلام.

نقل رئيس المجلس الأعلى للشئون الإسلامية في أثيوبيا الشيخ حاج إبراهيم توفا رسالة “تهنئة” إلى جميع الإثيوبيين وأصدقاء إثيوبيا بشأن التوصل إلى اتفاق السلام فيالمحادثات التي جرت بجنوب افريقيا من أجل إنهاء الحرب التي دارت بشمال أثيوبيا .

وذكر الشيخ أنه يجب على جميع الإثيوبيين العمل بجد معًا من أجل السلام الدائم لبلدنا بغض النظر عن الجنسية والعرق واللون والدين. ودعا الله الرحمة لمن فقدوا أرواحهم بسبب الحرب وأن يلهم اسرهم الصبر .

وكمادعا المسلمون إلى المشاركًة الفعالة في عملية إعادة تهجير أولئك الذين شردوا من قراهم حسب البرنامج والإجراءات التي تعد من المجلس الأعلى للشئون الإسلامية الأثيوبية .

ويظهر البيان أنه تم تقديم الشكر الجزيل للقادة الأفارقة والمفاوضين الممثلين والاتحاد الأفريقي الذي سهل المفاوضات التي استمرت 10 أيام في جنوب إفريقيا على أساس مبدأ ( حل المشاكل الإفريقية إفريقيا).

Share This:

Leave Your Comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

EIASC Copyright© 2022