-
Fajr
Salat:4:04 AM Time:5:00 AM -
Zuhr
Salat:12:09 PM Time:1:30 PM -
Asr
Salat:4:15 PM Time:4:45 PM -
Magrib
Salat:6:22 PM Time:6:22 PM -
Isha
Salat:7:38 PM Time:8:15 -
Jumuah
Salat:12:09 PM Time:1:30 PM -
Juma'ah
Start: 1:30 PM Iqamah: 2:00 PM














የፕሬዚደንቱ መልዕክት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
ውድ እና የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ሆይ።
ከሁሉ አስቀድሜ የአላህ ሰላም እና እዝነት በእናንተ ላይ ይሁን…አሰላሙዓለይኩም ወራሕመቱሏሂ ወበረካትሁ እላለሁ፡፡
እስልምና በመጨረሻው መልዕከተኛ ነብዩ ሙሐመድ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (ሰ.ዓ.ወ) ለሰው ዘር በሙሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰበከው በመካ ምድር ነበር፡፡ ከመካ ውጭ እስልምና የረገጣት የመጀመሪያዋ ምድር አገራችን ኢትዮጵያ ናት፡፡ ኢትዮጵያዊ ሙስሊምነታችን እስልምና ገና በአንቀልባ ጊዜው ላይ ሳለ ይጀምራል፡፡ በነብዩ ሙሐመድ ሶዓወ ልጅነት፡ እድገት፡ የእስልምና አስተምህሮት፡ መከራ፡ ድሎት፡ እና ሕልፈት ውስጥ ሁሉ ያለፍን ታሪካዊ ህዝቦች ነን፡፡
አትዮጵያዊያን እና እስልምና ትስስራቸው ታሪካዊ ቢሆንም በአገራችን በአራቱም ማዕዘናት ከነበሩት ገናና ኢስላማዊ ግዘቶች እና አስተዳደሮች መክሰም በተለይም ከአፄዎች የክርስትያን ሥርዓቶች መስፋፋት ወዲህ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ተቋማዊ አደረጃጀት አልነበራቸውም፡፡ የአሰከፊ ዘመናቱ የሙስሊሞች ቀዳሚ አጀንዳ ህልውናን ማረጋገጥ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በእምነታቸው ጥላ ስር በአንድነት በመሰባሰብ ተቋም መስርተው መኖር የጀመሩት እግጅ ዘግይቶ ክርስትያናዊ የአፄዎቹ አገዛዝ ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ተወግዶ ኢትዮጵያ አገራችን የሁላችንም እኩል አገራችን ከሆነችበት ከአብዮቱ ፍንዳታ በኋላ ነው፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ጉባኤ በመባል የሚታወቀው የመጀመሪያው የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ተቋም መጋቢት 4 1968 ዓ.ል በቀደምት አባቶቻችን ከፍተኛ ተጋድሎ በይፋ ተመሰረተ፡፡
Read MoreOur Press Release

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር የሞጣ ሙስሊሞች መልሶ ማቋቋም እና የልማት ፅ/ቤት የተሰጠ መግለጫ
- November 5, 2022
- By admin
...
View Details
Our Services

Pillars of Islam

-
ሸሃዳ
(Faith) -
ሶላት
(Prayer) -
ጾም
(Fasting) -
ዘካት
(Almsgiving) -
ሐጅ
(Pilgrimage)
Current Leaders
