ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና ሕዝብ ምስጋና አቀረቡ

ጥቅምት 21/2015

በድሬዳዋ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አዘጋጅነት በተካሄደው የትውውቅ መድረክ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማው ህዝበ ሙስሊም በስታዲየም በመገኘት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ጋር ትውውቅ አካሂዷል::

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በዚሁ መድረክ ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና ህዝብ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ አባላት ላደረጉት ደማቅ አቀባበል በራሳቸውና በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

ይህ ደማቅ አቀባበል የክልሉ አስተዳደርና የከተማው ነዋሪ ለኡለማዎች ያለውን ክብር ያሳየ እንደነበር ያወሱት ፕሬዘዳንቱ ይህም በጠቅላይ ምክር ቤቱ የማይረሳ ታሪካዊ ቀን ነው ብለዋል።

የትንሿ ኢትዮጵያ የፍቅር ተምሳሌት የሆነችው ድሬ ደዋ ለእንግዳ አክባሪ ነዋሪዎቿ: ለአንጋፋ የዕዉቀት ባለቤት ለሆኑ መሻኢሆች ለክቡር ከንቲባ ከድር ጁሐርና ለካቢኔ አባላት ለፀጥታ አባላት ክብርና ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

قدم رئيس المجلس الأعلى للشؤون الإسلامية الإثيوبية الشكر لإدارة مجتمع شعب دريدوا

20/02/15

شكر رئيس المجلس الأعلى للشؤون الإسلامية الإثيوبية ، الشيخ حاج إبراهيم توفا ، نيابة عن نفسه واللجنة التنفيذية بالمجلس لمجتمع إدارة دريدوا على الترحيب الحار الذي لقيه المجلس الأعلى للشؤون الإسلامية .

وذكر الرئيس أن هذا الاستقبال الحار أظهر احترام الإدارة بدريدوا وأهالي المدينة للعلماء وقال إن هذا يوم تاريخي لن ينساه المجلس الأعلى.

دريدوا هي اثيوبيا الصغيرة،و رمز الحب ،ودريدوا هي مثل عليا في الإحترام والإمتنان لسكانها الكرام والعلماء القدامى والعمدة الموقر خضر جوهر وأعضاء مجلس دريدوا و أمنها.

Share This:

Leave Your Comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

EIASC Copyright© 2022