ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ከፈረንሳይ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

ጥቅምት 18/2015

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር የሆኑትን ሚስተር ሬሚ ማሬሾ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል::

የፈረንሳይ አምባሳደር በጠቅላይ ምክር ቤቱ በተገኙበት ወቅት ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት በተጨማሪ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ፀሃፊ ሼይኽ ሐሚድ ሙሳ እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ከማል ሀሩንም ተገኝተዋል::

በቆይታቸውም ከጠቅላይ ምክር ቤቱ አመራሮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል::

Share This:

Leave Your Comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

EIASC Copyright© 2022